ቀና አታርጉኝ እኔን
ከሄደች ትታው መማፀኔን
[Verse 1]
ተክዤ ልግፋው ይህ ሀዘኔን
ጨለማ አልብሳው ስትሄድ
የፈካው ቀኔን
እኔስ አቅም የለኝም
እባክሽ ብዬ ልመልሳት
ቢፈጀው ልቤን የፍቅር እሳት
[Pre-Chorus]
አይሞከርም መቼም እሷን ለመርሳት
ስትሄድ ስለያት አሄ ስሰናበታት
[Chorus]
ማን አወቀልኝ ውስጤን እንደምወዳት?
ልሸኛት እንጂ የሆዴን ችዬ
ባይል ነው ከላይ ግዴለም ብዬ
[Verse 2]
ገና በጊዜ በቀየው አድባር አብረን አድገን
ክፋት በሌለው በንፁህ ፍቅር ተፈላልገን
ተዋደን ኖረን ባልነበረ አይነት በሚያስቀና
[Bridge]
ልቧን ከልቤ ድንገት ለያየን ቀን መጣና
በደለኛ ሰው ይቅርታ ብሎ አንሶ ሰው ከካሰ
[Chorus]
ይኖር ወይ ልቡን ያልመለሰ?
ሳይገባኝ ለኔ የቱጋ እንደሆን እንኳን ማስቀየሜ
ተይ ብያት ነበር ባለኝ አቅሜ
[Verse 3]
መማፀኔ
ማሪኝ ማለቴ
ለኔም ሳይገባኝ ነው ጥፋቴ
ታዲያ እንዴት ይሆን ወዳጅን ነግሮ
[Chorus]
ልብን መመለስ ወደ ድሮ?
ቀና አታርጉኝ እኔን
ከሄደች ትታው መማፀኔን
[Outro]
ተክዤ ልግፋው ይህ ሀዘኔን
ጨለማ አልብሳው ስትሄድ
የፈካው ቀኔን
እኔስ አቅም የለኝም