ብርሀን ይፈሳል ካለሽበት ቦታ:
ልዩ ነው ሳቅሽ የልብ እርካታ።
ባይንሽ ብታዪኝ ድክም አልኩልሽ፡
ሁለመናዬ ተረታ በግርማ ሞገስሽ።
ሄሄሄሄሄሄ
እእዬዬዬዬ
ጨዋታው ሞቋል ባንቺ መገኘት፡
መቼም አይጠገብ አንቺን መከተል።
ያንቺማ ፍጥረት መአዛው ይሸታል፡
ፍቅርሽ በልቤ ውስጥ ስር ሰዶ ይኖራል።
አንቺዬ የኔ አለም፡
ካንቺ በላይ የሚያምር የለም።
ረጋ ብለሽ ፈገግ ብትዪ፡
ጨለማው ይበራል ስትታዪ።
አንቺዬ የኔ አለም፡
ካንቺ በላይ የሚያምር የለም።
ረጋ ብለሽ ፈገግ ብትዪ፡
ጨለማው ይበራል ስትታዪ።
ሁሁሁሁሁ
ልክ እንደ ጽጌረዳ፡
እንደ ማለዳ ጠል።
ላንቺ ያለኝ ፍቅር፡
ሁሌም ይለመልማል።
በደስታ ተቀምጠሽ ብታወጊኝ ከልብሽ?
እኔም እሆናለው ዘላለም ወዳጅሽ።
አንቺዬ የኔ አለም፡
ካንቺ በላይ የሚያምር የለም።
ረጋ ብለሽ ፈገግ ብትዪ፡
ጨለማው ይበራል ስትታዪ።
አንቺዬ የኔ አለም፡
ካንቺ በላይ የሚያምር የለም።
ረጋ ብለሽ ፈገግ ብትዪ፡
ጨለማው ይበራል ስትታዪ።
አንቺዪ............ የኔ አለም
ረጋ ብለሽ.......... ፈገግ ብትዪ
አንቺዪ.......... የኔ አለም
ረጋ ብለሽ .........ፈገግ ብትዪ