[Verse 1]
አይመልስሽም ወይ የወሰደሽ መንገድ
ባያመጣሽ እንኳን ወይ እኔን ይዞ ይሂድ
ኪያ ናፍቀሽኛል
ዉዴ ናፍቀሽኛል
ጭንቅ ብሎኛል
[Verse 2]
ዉድዬ ትኖራለችና አንቺ ባለሽበት
ትላከኝ ጨረቃ ብታገኝሽ ድንገት
ክዋክብቶችን ልላክ ቢያገኙሽ ፈልገው
የኔ ዓለም ጠፍታለች እንዴት ልበላቸው
[Chorus]
ኪያ ናፍቀሽኛል የልቤ ትርታ
ድምፅሽ ነው የናፈቀኝ የነፍሴ ደስታ
መንገዱ አልመለሰሽ ወይ አልሄድኩበት
እንዲው ለብቻዬ ተቀጣው በናፍቆት
[Verse 3]
ይላኩኝ እንደሆን የሰማይ አእዋፋት
ዱካሽን ቢያስሱ የምድር አራዊት
ያገኙሽ እንደሆን ምን ብዬ ላዉራቸው
ውድዬ ፈልጓት እንዴት ልበላቸው
መንደርተኛው ሁሉ ደናነች እያሉኝ
ሆዴን ያስብሱኛል ኪያ መልስ አጣሁኝ
[Chorus]
ዉዴ ናፍቀሽኛል የልቤ ትርታ
ድምፅሽ ነው የናፈቀኝ የነፍሴ ደስታ
ኪያ ናፍቀሽኛል
ዉዴ ናፍቀሽኛል
ጭንቅ ብሎኛል