ግጥምና ዜማ አንሳር ከማል መርካቶ
(አዝማች)
ተመረቅኩኝ ዛሬ ደስ የሚል ቀን፣
ጓደኞቼ ሁሉ አብራችሁኝ ሁኑልኝ።
እንጨፍር እንዝፈን ምርቃቴ ነው፣
የእኔ ምርቃት ነው ጨፍሩ እልል በሉ።
(፩ኛ ስንኝ)
ሻማው ይብራ አሁን ይብራ፣
ቀኑ ደምቋል ከእኛ ጋራ።
ኬኩ ይቆረስ ይቅረብ ወደ እኛ፣
ዛሬማ የለም የሚተኛ።
ተመረቅኩኝ ዛሬ ደስ የሚል ቀን፣
በምርቃቴ ዛሬ ደስ ይለኛል!
(፪ኛ ስንኝ)
ርችቱ ተሽ ተሽ ይበል ወደ ላይ፣
ደስታችን ይውጣ እስከ ሰማይ።
ጓደኞቼ እልል በሉ፣
አብረን እንሰንብት በሙሉ፤
እንጨፍር ምርቃቴ ነው፣
የእኔ ምርቃት ነው ጨፍሩ።
(፫ኛ ስንኝ)
እንጨፍር አብረን እንጨፍር፣
በደስታ በሳቅ እንኑር።
እንኳን ደስ አላችሁ በሉኝ፣
ጓደኞቼ ኑ አቅፉኝ።
ተመረቅኩኝ ዛሬ ደስ የሚል ቀን፣
እንሰንብት አብረን እንደሰት!