ደስታ ተመልሷል ለአንችው ነው ልብ ተጨንቋል
ቀናቶች ቢረዝሙ ቢቆጠሩ አመታት
ግዜ ቢለያየን ቢያልፊብን ዘመናት
ከልብሽ ብጠፋም ከትውስታሽ ጓዳ
በስቃይ ታስሬ በናፍቆት ስጎዳ
ህልሜም ባይሳካ ይህንን ባላገኝ
በደስታየ ዘመን ባይቴዋር ብያረገኝ
ግድ የለም ችላለው ሁሉንም ችየ
እጠብቅሻሌው ልብን አባብየ
ምን ያደርግልኛል ካንች ወድያ ኑሮ
ፍቅርሽ ይበቃኛል የስንቅሽ ቋጠሮ
በትዝታሽ ዋሻ እራሴን ደብቄ
በምናቤ ስየ ፍቅርሽን ሰንቄ
ሳትወጅኝ ወድጄሽ
ግን አንችእንደት ነሽ
እንዴት ነሽ የልበ ንግስት አንችው ነሽ
አስብሻለው ከጠዋት እስክመሽ
ምን ነበር ባልነግርሽ
እኔ እንደምወድሽ