[Verse 1]
ይረገም ይረገም
ይህ እግሬ አልፎ የሄደበት ይረገም
ይህ ጎኔ ሄዶ የተኛበት ይረገም
ይህ ጥርሴ ሄዶ የበላበት ይረገም
[Verse 2]
ይህ ልቤ ሌላ ያሰበበት ይረገም
ይህ ክንዴ ሌላ ያቀፈበት ይረገም
ከንፈሬ ሌላ የሳመበት ይረገም
ያይኔ ነገርማ ገና ብዙ አለበት
[Chorus]
እሷ ወዲያ ሆና የልቤ አይደርስልኝ
እስኪ ወዲህ ትምጣ ትግባ ትደባብሰኝ
እንደ ቄሱ ጭራ እንደ እንዝርቷ ብናኝ
ይሄው መጣሁላት ትግባ ትደባብሰኝ
[Verse 3]
መላመድ ነው እንጅ መራቅ የት ተገኝቶ
እንግዲህ ከልፍኙ ካዳራሹ ገብቶ
ሰፊው መንገድ ሳለ ለመመላለሻ ዘግቶ
ልቤን አረገችው መነሻ መድረሻ ታገኘው
[Chorus]
እሷ ወዲያ ሆና የልቤ አይደርስልኝ
እስኪ ወዲህ ትምጣ ትግባ ትደባብሰኝ
እንደ ቄሱ ጭራ እንደ እንዝርቷ ብናኝ
ይሄው መጣሁላት ትግባ ትደባብሰኝ