ሃይ ሙባ ነኝ
የጅማ ልጅ
እንግዲ ከራስ በላይ ምን አለ
ወዳጅ መስሎ ጠላት አለ
ሰዉን ቀርበህ ተረዳው
እንደቀበሮ ቀብረህ አትገምተው
ዝም ያለ ዉሃ ጥልቀት እንዳለው ሁሉ
የኔም ሂወት ጥልቅ ናት ለመፍረድ እንዳቾኩሉ
ስንቱን አየሁት ቀርቤው
ያየሁት የታየኝን አየው
ልክ እንደዛው ማንነቱን ገመቸው
አንዳንዴ ሰው ቃሉ ሳይሆን ተግባሩ ነው መጽሐፍ
ሪላክስ ሪላክስ
ያወከኝ እንድታውቀኝ የፈቀድኩልህን ብቻ ነው
ከንብ ማርን እንደምጠብቀው
እኔም ላንተ መስታወት ነኝ
መልካሙን በመልካም
ነገሩን በፍቅር አርቃለው
አዎ እኔ ልጅ ሙባ
ያ የአባጅፋር `የጅማ ልጅ
በኔ ማንነት ማንም ሊሆን አይችልም
በድንጋይ ሚዛን ወርቅ ሊለካ አይቻልም
ሪላክስ ሪላክስ
ያወከኝ እንድታውቀኝ የፈቀድኩልህን ብቻ ነው
ሰው በማንነቱ ተማምኖ ብኖር
የከፍታው መሰላል ወደ ሰማይ ነው