[Verse 1]
ልክ እንደ ቀሚሷ
ጉፍታዉ ቅጠልያ ፡ መፋቂያዋ ወይራ
የግንባሯ ጸዳል ፡ ቅንድብ ያይኗ ጭራ
አቅሏ ታክሎበት ፡ ማማሯ የሚያስፈራ
ሁሌም የሚያጓጓ ፡ ሁሌም የሚናፈቅ ፡ ልክ እንደ ከተራ
[Chorus]
መገን
ቀለሟም መጋላ ፡ እጅጉን ደርባባ
ቢተዉት የማይተዉ ፡ ሊይዝ የሚያደባ
የውበት ደረጃ
[Verse 2]
በስለታም ቁሶች ፡ ቢለካ ተለቆ
ማማር ስለት አለዉ ፡ ልክ እንደጥልቆ
ዛጎል እንዳስጌጠዉ ፡ የኩሌ ጦር ዛቢያ
ተስሏል ያሰኛል ፡ እንደዝናር ካሪያ
[Chorus]
መገን
ቀለሟም መጋላ ፡ እጅጉን ደርባባ
ቢተዉት የማይተዉ ፡ ሊይዝ የሚያደባ
የውበት ደረጃ
[Bridge]
እንኳንስ በጸሐይ ፡ በቀን በጠራራ
ስንድድ በሚያሰካዉ ፡ ላንገት ዉበት ሃድራ
በምሽት ጨረቃ ፡ ወበቅ በሌለበት ፡ በብርሃን ብራ
አክናዷ እንደ ጥርኝ ፡ ትንፋሿ እንደ ናትራ
በድቅድቅ ጨለማ ፡ ከሩቅ የሚጣራ
[Chorus]
መገን
ቀለሟም መጋላ ፡ እጅጉን ደርባባ
ቢተዉት የማይተዉ ፡ ሊይዝ የሚያደባ
የውበት ደረጃ
[Outro]
መገን ይሁን ወሎ ፡ እንበል ለሱ መገን
ቁመቷ መለሎ ፡ አንገቷ እንደ ሰጎን
ጣይ ለሞቀዉ ማማር ፡ ሩህ ለሚያሳምን
አጃኢብ ነዉ ማለት ፡ አሁን ነው መጀገን
መገን