intro]
አይፍቀውም ውለታሽን ህሊናዬ
አይክደውም ስጦታሽን ልቦናዬ
አንደበቴ አይቀጥፍም
ቃሌ አይታጠፍም
ከቶ አይዛነፍም
[verse 1]
ለኔ የሆንሽልኝን እንዴት እረሳለው
እስከ ዕለተ ሞቴ አስታውሰዋለው
የኔነቴን ክብር የኔነቴን ግርማ
ጤነኛ አይደለውም ከጠላሁሽማ
ለፍቅር የከፈልሽው ውድ ዋጋ
በክብር ይኖራል እኔው ጋ
ልብሽ ይተማመን አይስጋ
[Chorus]
ላልጠላሽ ቃል አለኝ
ላልከዳሽ ቃል አለኝ
ካላንቺ ማን አለኝ
(Repeat x2)
[Verse 2]
ዝም ይላል ወይ ሰውስ?
ጎረቤት ሰፈሩ ምን ነካሽ
ጉድ ይላል ሀገሩ
ጉድ ይላል መንደሩ ብከዳሽ
ሰው አያረገኝም በጭራሽ
[Bridge]
በእውነተኛ ልብሽ አንቺ እያፈቀርሽኝ
እንዴት ይጠላኛል ብለሽ ጠረጠርሽኝ?
ውስጤን ባየሽልኝ ገብተሽ ባነበብሽው
የመውደዴን መጠን ልኩን ባገኘሽው
ምን ግዜም የማይጎል እምነቱን
ባወቅሽው የልቤን ፅናቱን
በተረዳሽልኝ እውነቱን
[Verse 3 / Outro]
አሁንም አሁንም ደግሜ ደግሜ ልንገርሽ
ራሴን አሳልፌ ሰጥቻለውና ለፍቅርሽ
እባክሽ በኔ እምነት ይኑርሽ
[Final Chorus]
ላልጠላሽ ቃል አለኝ
ላልከዳሽ ቃል አለኝ
ካላንቺ ማን አለኝ
(Repeat until fade out)