(slow intro music)
ጎልት በሚታየው... በዝግታ መሃል
ጥልቅ ስብእና.. ትህትና ይነበባል
ብትቆጥቢ ቃላት.. ከአይንሽ ብዙ ይታያል
ለቁጥብ ማንነት መገዛት ያኮራል።
አንች የድንገት ሌባ ዬ
ጠፋ ልቤ ከገላ ዬ
ፌሽታ ከተመቸሽ?
የቀረሽ ገላ ዬን ጠቅለሽ በወሰድሽ።
(guitar solo)
ውበትሽ መልክ አይደል... የልብ ብርሃን ነው
ሰው በመሆን ብቻ... ገኖ የሚታየው።
በቁንጅና አትታቢ... ግርማሽ መገራት ነው
ድንገት ባይ ወደድኩሽ... ተፈጥሮሽ ልዩ ነው።
ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ
አንች የድንገት ሌባዬ
ጠፋ ልቤ ከገላዬ
ፌሽታ ከተመቸሽ?
የቀረሽ ገላ ዬን ጠቅለሽ በወሰድሽ።
ኡኡኡኡኡ
እንደ ንጋት ጀምበር... በርጋታ የፈካሽ
በገዛ ውበትሽ... ያልታለልሽ ያልታበይሽ
ከመቶ ዎች መሃል... አንቺ ተለይተሽ
በሰውነት ብቻ... ያሸነፍሽ የገዛሽ።
(solo)
አንች የድንገት ሌባ ዬ
ጠፋ ልቤ ከገላዬ
ፌሽታ ከተመቸሽ?
የቀረሽ ገላ ዬን ጠቅለሽ በወሰድሽ።
(outro)
ድንገት ያገኘሁሽ... እድል ስጦታዬ
እንደ ወርቅ የጠራሽ... የነፍስ እርካታዬ
እንዲሁ በዝምታሽ... ልቤን ወስደሽዋል
ለሰውነትሽ ክብር... ልቤ ተገዝቶልሻል።
(melody)