በሰላምታ ሰበብ ልጥራክ እስቲ ማሬ
አንተ እንደው አይገባህ ይህ ምስኪኑ ፍቅሬ
እስቲ እሺ በልና ቀርበን እንጫወት
ፍቅርና ከሀገር ልጅ ጋር ቢሆን ምን አለበት
አስተውለክ እየኝ እኔ እወድሀለሁ
ሀሳብ እምነቴንም ላንተ ሰጥቻለሁ
ቀርበከኝ የውስጤን ብታየው ምናለ
ካንተ ውጪ ሌላ አይኔም ተከለለ
ውይይይይይይ ፍቅር እንዲ ነው ወይ
ኩራቴን አጥፍቶ አድርጎኝ ወላዋይ
ከዛሬ ነገ እያልኩ አልግደል ጊዜዪን
አንተም የኔ ሆነህ ላጋራ ደስታዬን
እኔን መሳይ ቆንጆዎቹ ላንተ ይገባሀል
በል ውሰደኝ ይኸው ልቤ ተሰቶካል
አአአአአአአገኘውት የፍቅሩን ይኸው ተሳካልኝ
ልበል እስኪ ልጁን የኔ አደረገልኝ