[Verse 1]
በምን ይካሳል የናት ውለታ
በደግነት ኣሳድጋን ለኛ ተንከራታ
ፍቅርዋ ሳይጎድልብን ሳይቀንስ ላአንድ አፍታ
ከክፉ ጠብቃን መከራዋን አይታ
እኛን እኛን ስትል አልቆ ሰውነትዋ ደብዝዞ ውበትዋ
ሚመጥን ስም አጣው ለዚ ማንነትዋ
ለእናቴ ለንፁ ልብዋ
[Chorus]
እማይ
ዝቅ ብዬ
ላመስግንሽ
ቢያንስብሽም ልስጥሽ ከበሬታ
እማ እናት
በምን ይካስ ያንቺስ ውለታ
ጤናና እድሜን ጨምሮልሽ
ያኑርሽ አንድዬ ጌታ
ሳቅሽ ይብዛ አይራቅሽ ደስታ
ውበትሽ ይፍካ
ያድልሽ ፈገግታ
ማም የኔ አለኝታ
[Verse 2]
ስታመም ተጨንቃልኝ
አቅፋኝ ፍቅር ሰታኝ
ተፈውሼ በእምባዋ ጠብታ
ጤና ብሆንላት ነው ለስዋ ደስታ
እኔን እኔን እያለች በልብዋ ትርታ
ኣሳድጋኛለች ስንት ስቃይ አይታ
[Chorus]
እማይ
ዝቅ ብዬ
ላመስግንሽ
ቢያንስብሽም ልስጥሽ ከበሬታ
እማ እናት
በምን ይካስ ያንቺስ ውለታ
ጤናና እድሜን ጨምሮልሽ
ያኑርሽ አንድዬ ጌታ
ሳቅሽ ይብዛ አይራቅሽ ደስታ
ውበትሽ ይፍካ
ያድልሽ ፈገግታ
ማም የኔ አለኝታ
[Bridge]
እኔ ነኝ ባለተራው እኔ ነኝ
የእናቴ ህመምዋ
እኔንም ይሰማኝ
እኔም ላግዛት ልሁን ከጎንዋ
ምርኩዝ ልሁናት በድካመዋ
ካፌም ከልቤም አይጥፋ ስምዋ
[Chorus]
እማይ
ዝቅ ብዬ
ላመስግንሽ
ቢያንስብሽም ልስጥሽ ከበሬታ
እማ እናት
በምን ይካስ ያንቺስ ውለታ
ጤናና እድሜን ጨምሮልሽ
ያኑርሽ አንድዬ ጌታ
ሳቅሽ ይብዛ አይራቅሽ ደስታ
ውበትሽ ይፍካ
ያድልሽ ፈገግታ
ማም የኔ አለኝታ
[Outro]
ማም ማሚዬ ማም
ማም ማሚዬ ማም
ማም ማሚዬ ማም
ማም ማሚዬ ማም
ማም ማሚዬ ማም
እማ እናቴ እማ
እማ እናቴ እማ
እማ እናቴ እማ
እማ እናቴ እማ
ደክማለች ለኔ
ደክማለች ለኔ
እናቴ ለኔ
ደክማለች ለኔ
ደክማለች ለኔ
እናቴ ለኔ